+ ማርያም እንወድሻለን +
ዘምሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ፥
እስመ ወለድኪ ለነ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን
ወስቴ ሕይወት ዘበአማን።
ማርያም እንወድሻለን ማርያም እንወድሻለን
ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን
ማርያም እንወድሻለን
ድክመቴን አትይው ማርያም
በኃጢአት መውደቄን ማርያም
ተስፋዬ አንቺው ነሽ ማርያም
እስከ ዕለተ ሞቴ ማርያም
ላልከዳሽ ምያለሁ ማርያም
ከስርሽ ላልጠፋ ማርያም
ገፀ በረከቴ ማርያም
የሕይወቴ ዋስትና ማርያም
የምእመናን ውበት ማርያም
ዘውድ አክሊላቸው ማርያም
ድንግል አንቺ እኮ ነሽ ማርያም
የመንገድ ስንቃቸው ማርያም
ምስክር ነኝ ለአንቺ ማርያም
እንደ ነቢያቱ ማርያም
ስጦታ መሆንሽን ማርያም
ለአዳም ልጆች ሁሉ ማርያም
ሞገስና ጸጋ ማርያም
በጌታ ፊት ያለሽ ማርያም
ከሰይጣን መሸሻ ማርያም
ዋስ ጠበቃችን ነሽ ማርያም
እንዴት ነበር ያኔ ማርያም
ጌታን ስትወልጂው ማርያም
የእረኞቹ ደስታ ማርያም
የመላእክት ዝማሬ ማርያም
ማርያም እንወድሻለን ማርያም እንወድሻለን
ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን
ማርያም እንወድሻለን
ስለወለድሽ የሕይወት ምግብን
ማርያም እንወድሻለን።
https://youtu.be/cFfEJm3VXIs
No comments:
Post a Comment