Thursday, May 19, 2022

ቅዱስ ገብርኤል ደጉ መልአክ

9-11-2014

"እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" --- ሉቃስ ፩፥፲፱

And the angel answering, said to him: I am Gabriel, who stand before God: and am sent to speak to thee, and to bring thee these good tidings. --- Luke 1:19

ኃያል ነህ አንተ

ትንቢተ ዳንኤል፤ ምዕራፍ ፫፥፩-፻
Daniel 3:1-100

ኃያል ነህ አንተ ኃያል 
ደጉ መልአክ ገብርኤል (፪)
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት 
አንተ ተራዳን በእውነት (፪)

በዱራ ሜዳ ላይ - - - ገብርኤል
ጣኦት ተዘጋጅቶ - - - ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ - - - ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ - - - ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ጸኑ
ጣዖቱን ረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ

ተቆጣ ንጉሡ - - - ገብርኤል
በሦስቱ ሕጻናት - - - ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ - - - ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት - - - ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
ከሞት አዳናቸው በእሳት ሳይነኩ

ከእቶኑ ስር ሆነው - - - ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ - - - ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው - - - ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ - - - ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር
አዩ መኳንንቱ የእግዚአብሔርን ክብር

ናቡከደነፆር - - - ገብርኤል
እጁን በአፉ ጫነ - - - ገብርኤል
ሠለስቱ ደቂቅን - - - ገብርኤል
ከእሳት ስላዳነ - - - ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከ መልአኩን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን።

ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
https://youtu.be/_0leJgcZ9dM

+++   +++   +++

ሰላም ለኪ እያለ

የሉቃስ ወንጌል፤ ምዕራፍ ፩፥፳፮-፴፰
Luke 1:26-38

ሰላም ለኪ እያለ (፪)
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ

ውኃ ስትቀጂ ክንፉን እያማታ
ሊያበሥርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ
ከሞገስሽ ብዛት (፪) ሲታጠቅ ሲፈታ
አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ።

የምሥራቹን ቃል ምሥጢር ተሸክሞ
ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደግሞ
እርጋታ ተሞልታ (፪) ነገሩን መርምራ
የመልአኩን ብሥራት ሰማችው በተራ።

ይደሰታል እንጂ መንፈሴ በአምላኬ
በምስጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ
ሐሳቤ ለቅፅበት (፪) ሌላ መች ያስባል
ለእኔ ልጅን መውለድ እንዴት ይቻለኛል?

ከአንቺ የሚወለደው ልዑል ነው ክቡር
የተመሰገነ በሰማይ በምድር
ምሥጢሩ ኃያል ነው (፪) ይረቃል ይሰፋል
ከአንቺ በቀር ይኽን ማን ይሸከመዋል?

ዕፁብ ነው ድንቅ ነው አንቺን የፈጠረ
አንቺን በመውደዱ ሰውን አከበረ
ዓለም ይባረካል (፪) በማሕፀንሽ ፍሬ
ክብርሽን አልዘልቅም ዘርዝሬ ዘርዝሬ።

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
https://youtu.be/AASHYqcWxcM

+++   +++   +++

አንድ እምነት ነው

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ 

አንድ እምነት ነው (፪)
ጽኑ ሃይማኖት ነው

ነቢያትን ትንቢት ሲያናግር የኖረው (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
ጽኑ ሃይማኖት ነው

አብርሃምን ለአምላክ ወገን ያደረገው (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
እርሱም ተዋሕዶ ነው

ለምግባረ ሠናይ መሠረት የሆነው (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
ጽኑ ሃይማኖት ነው

ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያወጣቸው (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
እርሱም ተዋሕዶ ነው

በሐዋርያት ላይ መንፈስን የላከው (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
እርሱም ተዋሕዶ ነው

ከእደ ረበናት ሶስናን የረዳት (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
ጽኑ ሃይማኖት ነው

ከአፈ አናብስት ዳንኤልን ያዳነው (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
ጽኑ ሃይማኖት ነው

እኛም በእምነት ጸንተን እንከተላቸው (፪)

አንድ እምነት ነው (፪)
እርሱም ተዋሕዶ ነው።

https://youtu.be/RJG_1Ze0LYo?si=cj2tVprZwCR9hP44

ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ፥ ዋይ ዜማ!
https://youtu.be/LcBZDUwesK8

No comments:

Post a Comment

OUR LADY OF LOURDES

OUR LADY OF THE IMMACULATE CONCEPTION + The visionary Bernadette Soubirous (Jan. 7, 1844 – Apr. 16, 1879) who was 14 years old at the time o...