ታኅሣሥ ፳፫ - በዓለ ዕረፍቱ ለቅዱስ ዳዊት፥ ንጉሠ እስራኤል
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ፤ ምዕራፍ ፲፮
I Samuel 16:10-13
፲ ፤ እሴይም ከልጆቹ ሰባቱን በሳሙኤል ፊት አሳለፋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፥ እግዚአብሔር እነዚህን አልመረጠም አለው።
፲፩ ፤ ሳሙኤልም እሴይን፥ የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፥ ታናሹ ገና ቀርቶአል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ። ሳሙኤልም እሴይን፥ እርሱ እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው አለው።
፲፪ ፤ ልኮም አስመጣው፤ እርሱም ቀይ፥ ዓይኑም የተዋበ፥ መልኩም ያማረ ነበረ። እግዚአብሔርም፥ ይህ ነውና ተነሥተህ ቅባው አለ።
፲፫ ፤ ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ፤ ምዕራፍ ፪፥፲፩
I Kings 2:11
ዳዊትም በእስራኤል ላይ የነገሠው ዘመን አርባ ዓመት ነበረ። በኬብሮን ሰባት ዓመት ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።
ንኡስ አነ እምአኀውየ
I WAS SMALL AMONG MY BROTHERS
A Psalm of Saint David, King of Israel
መዝሙር ፡ ዘርእሱ ፡ ዘዳዊት ፡ ዘጸሐፈ ፤ ወውፁእ ፡ ውእቱ ፡ እምኈልቍ ፤ ዘአመ ፡ ይትበሐቶ ፡ ወይትበአስ ፡ ምስለ ፡ ጎልያድ ፡ ወይቤ ፤
1 ንኡስ ፡ አነ ፡ እምአኀውየ ፡
ወወሬዛ ፡ በቤተ ፡ አቡየ ፤ ወእሬዒ ፡ አባግዐ ፡ አቡየ ።
2 እደውየ ፡ ይገብራ ፡ መሰንቆ ፤
ወአጻብዕየ ፡ ያስተዋድዳ ፡ መዝሙረ ።
3 መኑ ፡ ነገሮ ፡ ለእግዚእየ ፤
ውእቱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ውእቱ ፡ ሰምዐኒ ።
4 ውእቱ ፡ ፈነወ ፡ መልአኮ ፡ ወአድኀነኒ ፤
ወነሥአኒ ፡ እምአባግዐ ፡ አቡየ ፡
ወቀብአኒ ፡ ቅብአ ፡ ቅዱሰ ።
5 አኀውየሰ ፡ ሠናያን ፡ ወልሂቃን ፤
ወኢሠምረ ፡ ቦሙ ፡ እግዚአብሔር ።
6 ወወፃእኩ ፡ ለተኣኅዞቱ ፡ ለሕዝብ ፡ ነኪር ፤
ወረገመኒ ፡ በአማልክቲሁ ፡ ርኩሳን ።
7 ወአንሰ ፡ ነሣእኩ ፡ ሠለስተ ፡ አእባነ ፡ እምውስተ ፈለግ ፡ ወወጸፍክዎ ፡ ውስተ ፡ ፍጽሙ ፡
አሜሃ ፡ ወድቀ ፡ በኃይለ ፡ እግዚአብሔር።
ወዓዲ ፡ ነሣእኩ ፡ ዘእምላዕሌሁ ፡ ሰይፈ ፡
ወመተርኩ ፡ ርእሶ ለጎልያድ ፤
ወአሰሰልኩ ፡ ጽእለተ ፡ እምደቂቀ ፡ እስራኤል ።
ወልደ ዳዊት ፥ አምላከ ዳዊት
ማቴዎስ ፳፪ ፥ ፴፫ - ፵፮
Matthew 22:33-46
ሕዝቡም ይህን ሰምተው በትምህርቱ ተገረሙ።
ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ አብረው ተሰበሰቡ።
ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው፥
መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው።
ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።
ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፥ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።
በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።
ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ፥ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት።
እርሱም፥ እንኪያስ ዳዊት፥ ጌታ ጌታዬን፥ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?
ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።
አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።
No comments:
Post a Comment